የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የዕርድ እንስሳት ድጋፍ አደረገ።

44

ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከተማ አሥተዳደሩ የፍልሰታ ጾም ፍቺን ምክንያት በማድረግ የዋጋ ግምታቸው 750 ሺህ ብር የኾኑ ሰንጋዎችን ድጋፍ አድርጓል።

የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የኮማንድ ፖስቱ አባል በድሉ ውብሸት ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

ማኅበረሠቡም ከሠራዊቱ ጎን በመኾን ለአካባቢው ሰላም መረጋገጥ የበኩሉን አሥተዋጽዖ እንደሚያደርግም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ማድረግ ይገባል” የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኅላፊ እና የጎንደር ቀጣና የኮማንዶ ፖስት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው
Next articleበላሊበላ ከተማ የተገኘውን ሰላም የበለጠ በማጽናት ጎብኝዎች በነጻነት ወደከተማዋ እንዲመጡ እየተሠራ መኾኑ ተገለጸ ።