
ባሕር ዳር: ነሃሴ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት “ከወንድሜ ሼክ ሙሀመድ ቢን ዛይድ ጋር የከፈትነው የሳይንስ ሙዚየም አውደ ርዕይ የሀገራችንን ከፍተኛ የውሃ እና የኢነርጂ አቅም ያሳያል!” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም የውሃ እና ኢነርጂ አውደ ርዕይ በይፋ ከፍተዋል።
የኢትዮጵያን የውኃ እና የኢነርጂ ሀብቶች እንዲሁም እምቅ አቅምን ለማሳየት ያለመው አውደ ርዕይ ለሚቀጥሉት ሳምንታት ለሕዝብ ክፍት ይሆናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!