
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የከተማዋ ኮማንድ ፖስት አባል በድሉ ውብሸት እንደተናገሩት ገደብ ተጥሎበት የነበረው የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ አገልግሎት ወደ ሥራ መመለሱን አስታውቀዋል።
ይህ የኾነው የከተማዋ ነዋሪዎች ባደረጉት የሰላም ግንባታ ጥረትና ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በተሠራው ቅንጅታዊ ሥራ ነው ብለዋል።
የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ባለንብረቶች በበኩላቸው ሥራ በማቆማቸው ለችግር ተዳርገው እንደነበር ተናግረዋል።
አሁን ከተማዋ ወደ መረጋጋት በመመለሷ ሥራ በመጀመራቸው መደሰታቸውን ለአሚኮ ገልጸዋል።
የግል ህይወትን ከመምራት እስከ ቤተሰብ ማሥተዳደር የሚደርስ ሥራ እንደሚሠሩ የተናገሩት አሽከርካሪዎቹ ሰላሙ በመመለሱ ከግለሰብ እስከ ሀገር ፋይዳው በዋጋ የማይተመን ነው ብለዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ ሁሉም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራዎቻቸው ተመልሰዋል የሚሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየተደረገ ያለው ውይይት ሰላም እንዲሰፍን ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።
የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት የከተማዋ ነዋሪ ተባባሪ እንዲኾንም ጥሪ አቅርቧል።
ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!