በአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የመንግስት ሠራተኛው ሚና ከፍተኛ ነው።

53

ደብረብርሃን: ነሃሴ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ሠራተኞች በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከኮማንድ ፖስቱ አመራሮችጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪና የኮማንድ ፖስቱ አባል አቶ መካሻ ዓለማየሁ በአማራ ሕዝብ ጥያቄ ላይ ልዩነት የለም ያሉ ሲሆን ጥያቄዎቹ ግን ሊፈቱ የሚገባው በሰላማዊ ንግግር መሆን አለበት ብለዋል።

የመንግስት ሠራተኛው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ሥራ አቁመው የነበረ ቢኾንም አሁን ሁሉም ወደሥራ እንዲመለሱ ተደርጓል ነው ያሉት አቶ መካሻ። ሠራተኛው ኀላፊነቱን በአግባቡ በመወጣትና የተዛባ መረጃን ከማሰራጨት በመቆጠብ ለጸጥታው መጠናከር ኀላፊነቱን መወጣት አለበትም ብለዋል።
በውይይት መድረኩ የሕዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ ለማድረግ ቅድሚያ ሰላም ያስፈልጋልና ለሰላም ቅድሚያ መሰጠት ይገባል ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበትራንስፖርት ችግር ምክንያት ነፍሰጡር እናቶች እና አቅመ ደካሞች ጉዳት ደርሶባቸዋል” የባጃጅ አሽከርካሪዎች
Next articleበተለያዮ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ግጭቶች በአካል ጉዳተኞች ፣ በህጻናት እና በሴቶች ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ መኾኑ ተገለጸ፡፡