በትራንስፖርት ችግር ምክንያት ነፍሰጡር እናቶች እና አቅመ ደካሞች ጉዳት ደርሶባቸዋል” የባጃጅ አሽከርካሪዎች

53

ባሕር ዳር: ነሐሴ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡

አሚኮ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች እንዳሉት በክልሉ የሰላም መደፍረስ ከተከሰተ ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት በመቆሙ ያገኙት የነበረው ገቢም ቆሟል፡፡ በዚህም በቤተሰቦቻቸው ላይ ኢኮኖሚያዊ ችግር አጋጥሟል ነው ያሉት፡፡ በተለይም ደግሞ ሕፃናት መጎዳታቸውን ነው ገልጸዋል፡፡ ነፍሰ ጡር እናቶች በባሕላዊ መንገድ እንዲወልዱ ተገደዋል፡፡ አቅመ ደካሞችና ህጻናትን ሕክምና ለማድረስ መቸገራቸውንም ነው ያነሱት፡፡

የባጃጅ ትራንስፖርት ክልከላ መነሳቱ በተለይ ደግሞ የታክሲ አገልግሎት ተደራሽ ባልኾነባቸው አካባቢዎች የማኅበረሰቡን የትራንስፖርት ችግር እንደሚያቃልል ገልጸዋል፡፡

ሰላም የሁሉም መነሻና መዳረሻ በመኾኑ አሽከርካሪዎች ሕግና ሥርዓትን አክብረው እንዲሠሩም ጠይቀዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰሞኑን ተከስቶ ከነበረው ችግር በመውጣት ወደ መደበኛ ሥራችን ተመልሰናል” የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ አርሶ አደሮች
Next articleበአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የመንግስት ሠራተኛው ሚና ከፍተኛ ነው።