በፍኖተ ሰላም ከተማ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

48

ባሕር ዳር: ነሐሴ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ባለፉት ቀናት የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት ረግቦ በከተማዋ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የተፈጠረውን ግጭት እና አለመረጋጋት ተከትሎ ከሰላም እጦት በተጨማሪ የንብረት ውድመት እና የሕይዎት መስዕዋትነትም መከፈሉን ነዋሪዎች ለአሚኮ ገልጸዋል።

ከትላንት ነሐሴ 9/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ አንፃራዊ ሰላም በመስፈኑ ነዋሪዎች በሰላም መንቀሳቀስ መጀመራቸውን ነው የነገሩን።

ከዛሬ ነሐሴ 10/2015 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ስለመጀመሩም ነዋሪዎች ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ወደ መደበኛ አገልግሎት የተመለሱ ተሽከርካሪዎች ቁጥር አነስተኛ ነው ተብሏል።

በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶችም ከትላንት ነሐሴ 9/2015 ዓ.ም ጀምረው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። አሁንም ድረስ ያልተከፈቱ ሆቴሎች እና ሬስቶራንቶችም አሉ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ።

አሁን ላይ በከተማው የሚያሰጋ የፀጥታ ችግር ባለመኖሩ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትና መስሪያ ቤቶች ያለስጋት ወደ መደበኛ ሥራቸው መግባት የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩንም ነዋሪዎች አስረድተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleግጭቱ በክልሉ ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ ላይ የፈጠረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከባድ መኾኑ ተገለጸ፡፡
Next articleበፀጥታ አለመረጋጋቶቸ ምክንያት ዕቅዱን ተከትሎ ሥራዎቹን ለማከናወን መቸገሩን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡