
ባሕር ዳር: ነሐሴ 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን በምትገኘው ቡሬ ከተማ ባለፉት ጥቂት ቀናት የሰላም መደፍረስ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል።
የከተማዋን አሁናዊ መረጃ አስመልክቶ ነዋሪዎች ለአሚኮ በሰጡት መረጃ መሰረት ቡሬ ወደ ቀደመ ሰላሟ እየተመለሰች ነው።
እንደነዋሪዎች ገለጻ አሁን ላይ የከተማዋን ሰላም የሚረብሽ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር የለም፤ የንግድ ቤቶች መከፈት ጀምረዋል።
የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ስለመጀመሩም ነዋሪዎች ገልጸዋል። ሙሉ በሙሉ ባይባልም ሆቴሎች፣ ካፌዎች እና ሬስቶራንቶች ከዛሬ ነሐሴ 9/2015 ዓ.ም ጀምረው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!