ደብረ ብርሀን ከተማ ወደ አንፃራዊ ሰላም ተመልሳለች።

77

ባሕር ዳር: ነሐሴ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን መቀመጫ የሆነችው ደብረ ብርሀን ከተማ ወደ አንፃራዊ ሰላም መመለሷን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ።

በከተማዋ የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በከፊል የጀመረ ሲሆን÷ ባንኮችና የግል የፋይናንስ ተቋማትም ስራ ላይ ናቸው፡፡

ከደብረ ብርሀን ከተማ ወደ ሌሎች ከተሞች የሚደረግ ትራንስፖርትም በአንዳንድ መስመሮች ስለመጀመሩ ፋና ባደረገው ምልከታ ማረጋገጥ ችሏል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ከተማዋን ወደ ተሟላ ሰላም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራ የጀመሩ መሆናቸውን ገልጸው፤ አመራሩ ከህዝብ ጋር ውይይት መጀመሩን አመልክተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዘላቂ ሰላም ለማጽናት ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
Next article“በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ለመቆጣጠር በትኩረት እየተሠራ ነው” የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት