የደብረታቦር ከተማ ሰላሟን አስጠብቃ መቀጠሏን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

109

ባሕር ዳር:ነሐሴ 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ደብረታቦር ከተማ ባለፉት ቀናት በተከሰተው አለመረጋጋት የከተማው ሕዝብ ችግር ውስጥ መቆየቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በተፈጠረው ችግር በከተማዋ ያሉ ሁሉም አገልግሎቶች ተቋርጠው ስለነበር ነዋሪው ችግር ላይ ወድቆም እንደነበር ነው ለአሚኮ የተናገሩት፡፡

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ፡-
👉 በተፈጠረው አለመረጋጋት ሀገር ሰላም ብለው ወጥተው የነበሩ ግለሰቦች ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡
👉 የነዋሪዎች ቤት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
👉 የሰው ሕይወት ጠፍቷል፡፡
👉 አቅመ ደካሞች፣ ሕፃናት እና እናቶች ለሥነ ልቦና ችግር ተጋልጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ሕዝቡ ሰላሙን ለመመለስ ባደረገው ጥረት የደብረታቦር ሰላም በአስተማማኝ ኹኔታ ላይ እንደሚገኝ ያረጋገጡት ነዋሪዎቹ ወደፊት እንዲህ አይነት ችግር እንዳይከሰት ጠንክረው ሰላማቸውን እንደሚጠብቁ አረጋግጠዋል፡፡
እንደነዋሪዎቹ ትዝብት፡-

✍️ አሁን ላይ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡
✍️ ባንኮችም በሥራ ቀናት አገልግሎት ወደመስጠት መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል፡፡
✍️ ሆቴሎች አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡
✍️ሱቆች ተከፍተው ነዋሪዎች ግብይት እየተካሄደ ነው።
✍️ ሰዎችም በነጻነት ወጥተው ይገባሉ፣ ወደእየ ሃይማኖት ተቋማቸው በነጻነት እየሄዱ እንደሚስተዋሉም ነዋሪዎቹ ትዝብታቸውን አጋርተውናል፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች ወደፊት የደብረታቦር ከተማን ሰላም ሊያውኩ የሚችሉ ነገሮችን እንደሚከታተሉ እና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ጥቆማ እንደሚሰጡም ነው ያረጋገጡት፡፡ ነዋሪዎቹ አሁንም ጸጉረ ልውጥ የኾኑ ሰዎችን እየተከታተሉ እየያዙ ወደ ሕግ እያስተላለፉ እንደኾነም ለአሚኮ በሰጡት መረጃ አብራርተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleገንዳውኃ ከተማ ወደሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች መኾኑን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
Next article“ሰላም ለላሊበላ የልብ ትርታ ነው” የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ዲያቆን ተፋራ ሰይፉ