ገንዳውኃ ከተማ ወደሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች መኾኑን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

71

ባሕር ዳር: ነሃሴ 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሰሞኑም ባጋጠመው የጸጥታ ችግር በነዋሪዎች ላይ በተለይም ደግሞ በእናቶች፣ አቅመ ደካሞችና ሕፃናት ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን አሚኮ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡ ይሁን እንጅ ከሰሞኑ ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት በጸጥታ ኃይሉና በሰላም ወዳዱ ማኅበረሰብ ችግሩ ተባብሶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ የግልና የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በከፊል ወደ ሥራ መግባታቸውን ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ ነዋሪዎች እንዳሉት አካባቢው ከፍተኛ የልማት ቀጣና ቢኾንም ለዓመታት በተከሰተው የሰላም መደፍረስ መልማት በሚገባው መጠን ሳይለማ ቆይቷል፡፡
ጦርነት ውድመት እና ጥፋት መኾኑን በመረዳት ማንኛውም ጥያቄ ያለው አካል በሕጋዊ መንገድ ማቅረብ ባሕል ማድረግ ይገባል ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፡፡

መንግሥትም የሚነሱ ጥያቄዎችን በውይይት እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡ ለሰላም የሚሠሩ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶችን ሥራ ማንኛውም አካል ዋጋ እንዲሰጥም ጠይቀዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጎንደር ከተማ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ መመለሷን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
Next articleየደብረታቦር ከተማ ሰላሟን አስጠብቃ መቀጠሏን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡