
አቶ ወርቁ አይተነው በሞጣ ከተማ አስተዳደር ከሰሞኑ የተቃጠሉ ቤተ እምቶችን መልሶ ለመገንባት የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ቃል ገቡ፡፡
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር መስጂዶች፣ ሱቆችና ቤተ ክርስቲያን ላይ ቃጠሎ መድረሱ ይታወሳል፡፡ የእምነት ተቋሟቱን መልሶ ለመገንባትም እንቅስቃሴ መጀመሩም የሚታወስ ነው፡፡
የእምነት ተቋማቱ ላይ የደረውን ጉዳት ዛሬ በሞጣ ተገኝተው የጎበኙት ባለሀብት አቶ ወርቁ ዓይተነው ለመልሶ ግንባታ የሚውል የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ቀል መግባታቸውን ከሞጣ ከተማ አስተዳደር እና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዝርዝር የድጋፍ አሰባበስ ሁኔታው ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ከሰሞኑ መረጃ የምናደርስ ይሆናል፡፡