የብላቴ ኮማንዶና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ኮማንዶዎችን እያስመረቀ ነው።

101

ባሕር ዳር: ነሃሴ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የብላቴ ኮማንዶ እና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል የተለያዩ አስቸጋሪ መሰናክሎችን ማለፍን እንዲሁም ፈጥኖ መድረስን ለሚጠይቁ ተልዕኮዎች ጠንካራ ስልጠና የወሰዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ኮማንዶዎችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ዛሬ እያስመረቀ ነው። የምርቃት መርሐግብሩን በማስመልከት ሰልጣኞቹ ያገኙትን ክህሎት በትልቅ የአምሳለ እውን ትርኢት አሳይተዋል።

በመርሐግብሩም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችን የማስተናገድ አቅም ኖሮት በማሰልጠኛ ማዕከሉ የተገነባውን አምፊ ቴአትር በይፋ ከፍተው በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኞችን ተክለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ ውኃ ተበክሏል እየተባለ የሚሠራጨው ወሬ ሀሰት መሆኑን የከተማዋ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት አስታወቀ።
Next article“ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል።