
ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ ውኃ ተበክሏል እየተባለ የሚሠራጨው ወሬ ሀሰት መሆኑን የከተማዋ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት አስታውቋል።
አገልግሎቱ ለአሚኮ እንደገለጸው በከተማዋ ውኃ ተበክሏል የሚለው መረጃ ፍጹም ከእውነት የራቀና ሕብረተሰቡን ለበለጠ አለመረጋጋት ለማጋለጥ ያለመ መሆኑን አስገንዝቧል።
የውኃ ተቋማት ላይ ጠንካራ ጥበቃ የሚደረግላቸው በመሆኑ ለእንዲህ አይነት ችግር የሚጋለጡ አይደሉም ነው ያለው አገልግሎቱ።
ይልቁንም በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት በተለምዶ እንፍራንዝ ተብሎ በሚጠራው የውኃው ምንጭ አካባቢ የመብራት ፖል በመውደቁ በከፊል ጉዶ ባሕር ሳይቶች ላይ የውኃ ምርት በመቋረጡ መሐል ከተማ እና ከፊል ቀበሌ 14 ውኃ ስለሌለ ችግሩ እንዲፈታ ከመብራት ኀይል ጋር እየተሠራ መሆኑንም ታውቋል።