ሁሉም በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በአስቸኳይ በማስቆም ወደ ሰላማዊ ውይይትና ምክክር እንዲመለስ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ።

178

ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በመግለጫቸው ስለሰላም አማራጭ ያነሷቸው ነጥቦች፦

👉የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ያለውን ችግር በሰላምና በውይይት ለመፍታት አሁን መረባረብ ይገባል፡፡

👉 የክልሉ የፀጥታ ችግር መንስኤ የኾኑትን በውይይት መፍታት አለብን ብለን በተደጋጋሚ ተናግረናል ብለዋል።

👉የሰላም ጉዳይ በክልሉ ምክር ቤትም አቋም ተወስዶ ተመራጮች በመሄድ ውይይት እያደረጉ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡

👉ማንኛውም ችግር በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ቢፈታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሰብዓዊ ኪሳራን ማስቀረት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

👉 የሰላም ዋጋው ከፍተኛ ስለኾነ ሁሉም ጥያቄ አለኝ የሚል ወገን ሁሉ ያለምንም ገደብ በየደረጃው እየተወያየ ችግሩን ለመፍታት መረባረብ ይገባል ፡፡

👉ከውይይት ውጭ ያለው ሂደት ክልላዊ ኪሳራ ከማምጣት ውጭ መፍትሔ እንደማያመጣም ተናግረዋል፡፡

👉ሁሉም ልዩነት ያለው አካል ነፍጡን አስቀምጦ ወደ ሰላማዊ ውይይት በመመለስ፣ በየደረጃው ወደ ተቋቋመው፣ የሀገር ሽማግሌ፣ የሃይማኖት አባት፣ የሕዝብ ተወካዮች፣ ወጣቶችና ሌሎች አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ችግሩ የሚፈታበትን አቅጣጫ ነድፎ መረባረብ ይገባዋልም፡፡

👉ለሰላም ዘብ በመቆም ልዩነታችንን አቻችለን፣ የሕግ የበላይነትን አስከብረን ችግሮቻችንን መፍታት ይገባናል፡፡

👉ሊመጣ የሚችለውን ክልላዊ ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ አሁኑኑ ለሰላም መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

👉አሁን ላይ በአንዳንድ አካባቢ ያለው ትንኮሳ እያደረ ሲሄድ ክልላዊ አለመረጋጋትና ሥርዐት አልበኝነት እንደሚፈጥርም ገልጸዋል፡፡

👉ክልሉን ለበለጠ አደጋ የሚጥል በመኾኑ ችግሩን የክልሉ ሕዝብ እንዲገነዘበውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

👉 ከችግር መውጣት አዳጋችና ከባድ መኾኑን ከሌሎች መማር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

👉እርስ በእርስ መገዳደል ለውጥ አላመጣልንም ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ሰላማዊ አማራጭን በመከተል ችግሩ እንዲፈታም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

👉ለሰላም ሁሉም እንደሚያገባው የተናገሩት ርእሰ መሥተዳድሩ በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በአስቸኳይ በማቆም ወደ ሰላማዊ ውይይት፣ ምክክር እንዲመለስ እና ክልሉ የተረጋጋ ኾኖ እንዲቀጥል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሕግ አግባብ መሠረት የክልሉ የጸጥታ መዋቅር እና የመከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ።
Next article“ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት ከኢንዱስትሪ ወጪ ምርቶች ከ450 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማግኘት አቅዳለች” የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል