
ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በመግለጫቸው ስለጸጥታ አካላት ያነሷቸው ነጥቦች፦
👉በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግሮች ተፈጥረዋል።
👉የጸጥታ ችግሩ የሰውን እንቅስቃሴ እየገታ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መኾኑን ነው ያነሱት፡፡
👉በግጭቱ በክልሉ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የኾነ ሰብአዊ ኪሳራ እያጋጠመ መኾኑንም አንስተዋል፡፡
👉የጸጥታ ችግር ሲያጋጥም የክልሉ የጸጥታ መዋቅርና የመከላከያ ሠራዊት ሕግ የማስከበር ተልእኮን እንደሚወጣ በየትኛውም ሀገርና መንግሥት የታወቀ መኾኑንም አንስተዋል፡፡
👉በሕግ አግባብ መሠረት የክልሉ የጸጥታ መዋቅር እና የመከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየሠራ ይገኛል፡፡
👉የጸጥታ መዋቅሩ እንቅስቃሴ የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ነው፡፡
👉 በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያልተገባ ስም መስጠት እና መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ መንዛት አስነዋሪ መኾኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል፡፡
👉የክልሉ የጸጥታ መዋቅርም ኾነ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበርና የሀገር አንድነትን ለማስጠበቅ ምሰሷችን ነው፡፡
👉የመከላከያ ሠራዊት ከሁሉም የሀገራችን ሕዝቦች የተውጣጣ፣ ሀገራዊ ቁመና ያለው ተቋም ነው።
👉የመከላከያ ሠራዊት ተቋም መመኪያችን በመኾኑ መደገፍና ማበረታታት ይገባል፡፡
👉የክልሉ የጸጥታ ኀይልም ኾነ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ተለያየ አካባቢ ሲንቀሳቀስ መተንኮስ ተገቢም ኾነ ሕጋዊ አለመኾኑን ገልጸዋል፡፡
👉 የክልሉ የጸጥታ መዋቅር እና መከላከያ ሠራዊት ሕግ ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉም የክልሉ ሕዝብ ከጎኑ በመኾን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!