
ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ጸሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ላይ ያተኮረ መሆኑን ባንኩ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመልክቷል።
የባንኩ ገዥ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢትዮጵያ እድገትን ለማፈጠን እና የኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲመጣ እየተወጣ ላለው ገንቢ ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!