
ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ የፈተና አሠጣጥ ሂደቱን ተመልክተዋል።
በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮነን፣ የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ.ር)፣ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ.ር) ጋር በመሆን በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታቸውም በሁለተኛው ዙር እየተሰጠ ያለው የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በጥሩ ሁኔታ እየተሠጠ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል።
ሐምሌ 25/2015 የተጀመረው የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እስከ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።
የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ምስጢራዊነቱና ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ይታወሳል። መረጃው የትምህርት ቢሮ ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!