
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ)
ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል ያስገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ወደ ሥራ አስገብታለች። የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ገንብተን በሥራ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመኾን ዛሬ ጠዋት በአንደኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በምርት ሥራ ላይ ካሉ ኢንዱስትሪዎቻችን ሁለቱን አብረን ጎብኝተናል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ብቻ ሳትኾን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ኹኔታን እየፈጠረች ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!