
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት ዛሬ የተጀመረውን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ የፈተና አሰጣጥ ሂደት ተመልክተዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኢንስቲቲዩት ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታቸውም ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በጥሩ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን ለመገንዘብ መቻላቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው ።
የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እስከ ሐምሌ 28/2015 ድረስ እንደሚቆይ መገለጹ ይታወቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!