
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከአማራ ክልል የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡
ከአማራ ክልል ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በሠላምና ፀጥታ አዝማሚያዎች ላይ በባህር ዳር ከተማ እየመከሩ ነው።
ክልላዊ ወቅታዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎችን እና የሠላምና የጸጥታ ሁኔታዎችን አመላካች መነሻ ሀሳብ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ቀርቧል።
የውይይት መድረኩ በወቅታዊ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎችና አዝማሚያዎች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የተጀመረው የሠላምና የልማት ሂደቱ እንዲጠናከር ፋይዳዉ የጎላ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል።
በሰላም እና በውይይት እንጂ በጦር መሳሪያ የተፈታ ችግር አለመኖሩ የተገለጸ ሲሆን የአማራ ክልል ሕዝብ ጦርነት ሳይሆን ልማት የሚሻ ሕዝብ በመሆኑ ልማቱን ይበልጥ በማተኮር የሕዝቡት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባልም ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!