ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድና የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ።

81

ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ዛሬ ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ችግኝ ተክለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፣ በሁለትዮሽ ውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

አጃይ ባንጋ በበኩላቸው፣ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም ኢትዮጵያ ለቁልፍ የልማት ግቦች የሰጠችውን ትኩረት አድንቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሜሪካ ገባ።
Next article“የኃይል አቀርቦት ችግር ለቡሬ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ማነቆ ኾኖበታል” አቶ ዳኛቸው አስረስ