
አዲስ አበባ: ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኀብረት ባንክ ከሳፋሪ ኮም ጋር የኤምፔሳ አገልግሎት ለመስጠት ባካሄደው የውል ስምምነት መሰረት ለደንበኞቹ ተገቢውን አገልግሎት ለመሥጠት እንደሚሠራም አስታውቋል።
ባንኩ የደንበኞቹን አገልግሎት ቀላል ለማድረግ እና የቅርንጫፍ ቢሮ በሌለባቸው የገጠር አካባቢዎች ተደራሽ እንዲኾን የሞባይል ባንኪንግን በሳፋሪ ኮም ኤምፔሳ ተደራሽ ለማድረግ በውል ስምምነቱ መሰረት እንደሚሠራ ተጠቅሷል፡፡
በቀጣይም ውሉን አጠናክሮ በመቀጠል ደንበኞች በጥሬ ብር ሳይኾን በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን ፈጣን ለማድረግ እንደሚሠራም ባንኩ ገልጿል።
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!