ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

49

ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርን ዛሬ ከሰአት በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታችው የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ሲሆን ኢኮኖሚያዊና የንግድ ግንኙነቶችን ለማሳደግ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ጉዳዮች ላይ ለመተባበር እንዲሁም በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ልማት ጉዳዮች ላይ ለመስራት ውይይት አካሂደዋል።

ስብሰባው መጠናቀቁን ተከትሎም በጠቅላይ ሚኒትር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ አብረው ችግኞችን ተክለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ በዘር ከተሸፈነው ሰብል ውስጥ 90 በመቶ የሚኾነው የእንክብካቤ ሥራ እንደተሠራ ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡
Next article“ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ኢንዱስትሪያል ፓርኩ ገብተዋል፡፡” የቡሬ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪያል ፓርክ