
ደብረማርቆስ: ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዞኑ በምርት ዘመኑ በሠብል ከሚለማው 607 ሺህ ሄክታር ማሳ 68 በመቶ በኩታ ገጠም አሠራር የሚለማ ሲኾን 212 ሄክታር በስንዴ ሰብል ይሸፈናል ተብሏል።
በዛሬው ክልላዊ የስንዴ ዘር መርኃ ግብር በዞኑ ከ5 ሺህ 2 መቶ በላይ ሄክታር ማሳ በስንዴ ሰብል እንደሚሸፍን ከዞኑ ግብርና መመሪያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአማራ ክልል በተያዘው የመኸር ወቅት በሠብል ለመሸፈን ከታቀደው 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ እስካሁን 3 ነጥ 5 ሚሊዮን ሄክታሩ በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።
በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ፣ የዞንና የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ዘጋ፡- ወንድወሰን ዋለ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!