የአማራ ወጣቶች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤውን በባሕር ዳር እያካሄደ ነው።

135

ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 19/2012ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ወጣቶች ማኅበር ‹‹አንደነት ለአማራ ወጣቶች ውበት፤ ለኢትዮጵያ ድምቀት›› በሚል መሪ ሐሳብ 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ለሁለት ተከታይ ቀናት በሚቆየው የአማራ ወጣቶች መደበኛ ጉባኤ ባለፉት ሦስት ዓመታት የነበረውን የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል። በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም ይመክራል።

በቀጣይ ሊሠሩ የሚገባቸውን አቅጣጫዎች ካስቀመጠ በኋላ ማኅበሩን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚመሩ የሥራ ኃላፊዎችን እንደሚመርጥም የወጣው መርሀ ግብር ያሳያል።

በውይይቱ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው። በሚኖራቸው ቆይታ የአጋርነት መልዕክታቸውን እንደሚያቀርቡም ነው የሚጠበቀው።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

Previous articleባሕር ዳር በተሽከርካሪ የሚፈጸም ስርቆት እና ዝርፊያ እንዲቆም ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡
Next articleዘመናዊነት በኢትዮጵያ ከየት ወደ የት?