መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የመጡ ምሁራን የዩኒቨርሲቲው መጠሪያ ስም የኾነውን የመቅደላ ተራራን ጎበኙ።

24

ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ከተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ምሁራን የዩኒቨርሲቲው መጠሪያ ስም የኾነውን የመቅደላ ተራራን ጎብኝተዋል።

መቅደላ አፋፉ ላይ ጩከት በረከተ፣
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ
እየተባለ ለዘመናት የሚዘመርለትን የአጼ ቴዎድሮስ ታሪካዊ ቦታን መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራኑ ባላቸው የዕረፍት ጊዜ ጉብኝት አካሂደዋል ፡፡

መቅደላ አምባ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማለትም ከ1855 እስከ 1868 እ.ኤ.አ የንጉሠ ነገሥታት እስር ቤት ማዕካለዊ ስፍራና የምሽግ ቦታ ኾኖ ከማገልገሉም በላይ አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር የተዋጉበትና ለጠላት እጅ አልሰጥም ብለው እራሳቸውን ያጠፉበት ቦታ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ለታሪክ መዘክርነት በቦታው የሚገኙት ከ6 እስከ 8 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሴባስቶፖል መድፍ፣ ከ2 እስከ 3 ሺህ ኪሎ ግራም የሚዝነው ትንሽ መድፍ፣ የአፄ ቴዎድሮስ ቤተ መንግስኬሥት፣ የእቃ ግምጃ ቤት፣ የቦይ ምሽግ፣ የመቅደላ መድኀኒዓለም ቤተክርስቲያን ፍርስራሾች እንዲሁም የአፄ ቴዎድሮስ የመቃብር ቦታ ይገኙበታል፡፡

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የመጡ ምሁራንም ይህንኑ ታሪካዊ ቦታ እና ቅርሶችን ነው የጎበኙት።

መረጃው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር የተገነቡ የአቅመ ደካማ ቤቶች ለነዋሪዎቹ ተላለፉ።
Next article30 ሚሊዮን በሚጠጋ ወጪ የተገነባው የናኒና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።