
ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዙር የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።
ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ከትናንት ጀምሮ በመቀበል ላይ ነው።
በወጣው የመግቢያ መርሃ ግብር መሰረት ቀሪወቹ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪወችን ዛሬ ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም እንደሚቀበል ዩኒቨርሲቲው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!