
ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሁለተኛ ዙር የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በዛሬው እለት መቀበል መጀመሩን እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።
በዚህ ዙር ከ6 ሺ 500 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በነገው እለት አጠቃላይ ገለጻ ተደርጎ ከማክሰኞ ጀምሮ ፈተናው የሚሰጥ ይሆናል።
ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ውጤት ተመኝቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!