
ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኮሌጁ በሁለተኛ ዲግሪ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት 528 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን በመጀመሪያ ዲግሪ 98 ተማሪዎች ናቸው የተመረቁት ።
የኮሌጁ ዲን ረዳት ፕሮፌሰር አባይነህ ክንዴ ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልእክት በብዙ ውጣ ውረዶች ተፈትናችሁ ለዚህ የበቃችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ብርሃን ኮሌጅ በአሁኑ ሰዓት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ተማሪዎችን ተቀብሎ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን እያከናወነ የሚገኝ ኮሌጅ መኾኑንም ገልጸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኀላፊ ዶክተር እዮብ አየነው እንዳሉት የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሰፊ ሥራ እየሠራ ይገኛል። በዚህ ሂደት ተሳትፋችሁ የተመረቃችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ኮሌጁ ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡ ሁለት ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል ሠጥቷል።ይህን እድል ያገኙ ተማሪዎችም በኮሌጁ ቆይታቸው ደስተኛ እንደነበሩ ገልጸዉ የእድሉ ተጠቃሚ በመኾናቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ገንዘብ ታደሠ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!