“ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት ያደረግነው የቢኩሎ ዓባይ የኮንክሪት ድልድይ ጠቀሚታው የላቀ ነው ” አቶ ሙሐመድ ያሲን

69

ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሜጫ ወረዳ ተገንብቶ በተጠናቀቀው የቢኩሎ ዓባይ ድልድይ ምረቃ የተገኙት የመንገድ ቢሮ ኀላፊ አቶ ሙሐመድ ያሲን ባለፉት ሦስት ዓመታት በብዙ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ተፅዕኖ፣ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነንም የልማት ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት አብቅተናል ብለዋል።

የመንገድ ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ለውጥና ውጤት ማምጣቱንም ገልጸወሰል። በእቅድ ላይ በመመሥረት ከፍፃሚ እና አስፈጻሚ ጋር በመግባባት ጠንካራ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት መከሰሄዱ ለውጥ እንዲመጣ አስችሏል ነው ያሉት።
ጠንካራ መስተጋብር በመፈጠር 541 ፕሮጀክቶችን በማቀድ 500 ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የመሠረተ ልማት ግንባታ በፍትሐዊነት ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አንስተዋል።

ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የቢኩሎ ዓባይ የኮንክሪት ድልድይም ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ድልድዩ የብዙ ፀጋዎች ባለቤት በሆነው በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫና በአዊ ብሔረሰብ ዞን ዳንግላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ኅብረተሰቦችን የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑም ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልጸዋል።

መረጃው የመንገድ ቢሮ ነው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባቲ ከተማ አሥተዳደር ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።
Next articleየላሊበላ ቅርስ በተመረጡ 22 ቦታዎች አስቸኳይ የጥገና ሥራ እየተካሄደለት ነው።