ከሚሴ: ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የባቲ ከተማ ከንቲባ ሰይድ መሐመድ ከ30 በላይ ፕሮጀክቶች ለምረቃ መብቃታቸውን ገልጸዋል።
ከተመረቁት ፕሮጀክቶች ውስጥ፦
👉 የጌጠኛ ድንጋይ መንገድ
👉 ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ መኪና
👉 ትምህርት ቤቶች
👉 የአንድ ማዕከልና የወጣቶች መዝናኛ ይገኙበታል ብለዋል ከንቲባው።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ በ2015 በጀት ዓመት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ፣ በውስጥ ገቢ፣ በዓለም ባንክ፣ በክልልና በፌዴራል መንግሥታት ድጋፍ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል ነው ያሉት።
👉 የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ሱለይማን እሸቱ ባለፉት አምስት ዓመታት በአማራ ክልል ውስጥ በዓለም ባንክ አማካኝነት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ ከ4ሺህ 100 በላይ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል ብለዋል።
👉 የባቲ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው ለአገልግሎት ክፍት የኾኑት ፕሮጀክቶች የኅብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ እንደነበሩገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሂም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!