
ወልድያ: ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሌጁ ከደረጃ ሁለት አስከ ደረጃ አምስት በማታና በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ650 በላይ ተማሪዎች ለ25ኛ ጊዜ ነው ያስመረቀው፡፡
የወልድያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ደረበ አያሌው ኮሌጁ ተማሪዎችን በተለያዩ ሙያዎች ከማሰልጠን ባሻገር በሥራና ስልጠና ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የሰልጠና እና የተለያዩ ድጋፎችን በመሰጠት ኀላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል ፡፡
ኮሌጁ ለተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት አቶ ደረበ ተመራቂዎችም በንድፈ ሀሳብና በተግባር ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው በተለያዩ የሥራ ፈጠራ ሥራዎች እንዲሰማሩ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የሥራና ስልጠና መምሪያ ኅላፊ አለምነህ ጌጡ የሀገር ውስጥን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሚናቸው የላቀ መኾኑን ገልጸዋል።
✍ መምሪያ ኅላፊው በዘርፉ የተመረቁ ዜጎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት ይደረጋልም ብለዋል፡፡
✍ ተመራቂ ተማሪዎችም የብድርና የመስሪያ ቦታ ከተመቻቸላቸው በሰለጠኑበት የሙያ መስክ በመሰማራት ለራሳቸውና ለሌሎች የሥራ እድል ለመፍጠር ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ባለ ዓለምየ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!