
ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አስተባባሪዎችና ፈታኞች ጣና ሐይቅን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝት መርሀግብሩ ጉብኝት የጣና ሐይቅ የጀልባ ላይ ሽርሽር፣ የገዳማት ጉብኝት ተጀምሯል።
ዓባይ እና ጣና መለያያ፣ ጉማሬ ፣ ክብራን ገብርኤል ገዳም፣ ዘጌ ኡራ ኪዳነምህረትና ሌሎችም ይጎበኛሉ።
በጉብኝቱ ከ750 በላይ ፈታኞችና አስተባባሪዎች እየተሳተፉ መኾኑን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!