ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል ገመድ አልባ የኔትወርክ ዝርጋታ እንደሚያካሂድ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናገሩ።

32

አዲስ አበባ: ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 13 ሚሊየን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል ገመድ አልባ የኔትወርክ ዝርጋታ እንደሚያካሂድ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናገሩ።

ኢትዮ ቴሌኮም የ2016 ዓመታዊ እቅድን አስተዋዉቋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬ ሕይወት ታምሩ እቅዱ የኢትዮ ቴሌኮምን የገበያ ላይ ድርሻ ያሳድጋል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ 998 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች እንደሚዘረጉ አስታዉቀዉ 140 የሚሆኑት በገጠራማ አካባቢዎች የሚዘረጉ ጣቢያዎች መኾናቸዉን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ የደንበኞችን ቁጥር በ8 ነጥብ 3 በመቶ በማሳደግ ወደ 72 ሚሊዮን ለማሳደግ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የ4G አድቫንስ 5G እና 3G የኔትወርክ አገልግሎትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሠራል ብለዋል።

የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችንም በ24 በመቶ በመጨመር ወደ 41 በመቶ ሚሊየን ለማሳደግ እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

የቴሌ ብርን ተደራሽነት በማስፋት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ላሉ ደንበኞች እንሠራለን ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የዲጅታል ፋይናንስን ለማሳደግ እንደሚሠራም ነው የተናገሩት።

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ 90 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ እንደሚሠራም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ:- ኤልሳ ጉኡሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢኒስቲቲዩት፤ ግብርና ሚኒስቴር እና የፈረንሳይ ልማት ተራድኦ ድርጅት ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በመተባበር በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next article“በዞኑ ከ4 መቶ 30 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመኸር ለማልማት እየሠራን ነው” የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ