የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ጎበኙ።

136

ባሕር ዳር: ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከተለያዩ ከተሞች እና ተቋማት የተወጣጣው የልዑካን ቡድን የካይሮ ከተማን የሕዝብ ብዛት መጨናነቅ ለማስተንፈስ መልሶ የማልማት እና ለወደፊቱ ትውልድ የሚሆን ዘመናዊ ፣ ሁለገብ እና ምቹ ከተማን ለመገንባት የተሠሩ ሥራዎችን ጎብኝቷል። ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት፤ ገጠርን ከከተማ አስማምቶ ለማደግ የተከናወኑ ተግባራትንም ተመልክቷል።

በጉብኝቱ ወቅት ከካይሮ ከተማ አስተዳደር ጋር ከተሞችን በማዘመን፣ ወቅቱን የዋጀ የከተማ እና የመሠረተ ልማት ግንባታን፣ እንዲሁም የተጨናነቁ የከተማ አካባቢዎችን ስለማስተካከል በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

ኢትዮጵያና ግብጽ በባህል፣ በታሪክና በሕዝብ ብዛት ተቀራራቢነት ያላቸው በመሆኑ የልዑካን ቡድኑ ያገኘው ልምድ በየከተሞቹ ሊተገበሩ የሚችሉ መሆናቸውን አባላቱ ገልጸዋል።

ጉብኝቱ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተከናወነ ነው።

በጉብኝቱ የፌደራል አመራሮች ፣ የአዲስ አበባ፣ የአዳማ፣ የባሕር ዳርና የሐዋሳ ከንቲባዎችም ተሳትፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከሱዳን ተሰደው በመተማ ወረዳ ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኞች ድጋፍ አደረገ።
Next article“በማንነታችን ላይ ዳግም ለአፍታ እንኳን ተዘናግተን የተራዘመ መከራ እና ባርነት ለመቀበል ፍጹም አንፈቅድም” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ