
ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሀገሪቱ በሚገኙ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት ተጀምሯል።
የማኅበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በዛሬው እለት ሀገር አቀፍ ፈተናውን በይፋ መውሰድ ጀምረዋል ።
የማኅበራዊ ሳይንስ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ከሐምሌ 19 ጀምሮ ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተናን እንደሚወስዱ ትምህርት ሚንስቴር መገለፁ ይታወቃል ።
በዛሬውም እለት የፈተናውን መጀመር አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የፈተናውን አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ8 መቶ 68 ሺህ በላይ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለጹ ይታወሳል።
ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ መሰጠት የጀመረው ፈተና በመጪው አርብ ሐምሌ 21 ቀን 2015 እንደሚጠናቀቅ እና በተመሳሳይ ሁኔታ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 25 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ. ም ድረስ ፈተናውን እንደሚወስዱ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመላክታል ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!