በሚቀጥሉት 6 ቀናት በአንዳንድ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከባድ እና እጅግ ከባድ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል ኢጋድ ገለጸ።

70

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን እና በሰሜን ምሥራቅ በኢትዮጵያ፤ በምዕራብ ኤርትራ፣ በምሥራቅ እና ደቡብ ምሥራቅ ሱዳን እንዲሁም በመካከለኛው የደቡብ ሱዳን አካባቢዎች ከባድ እና እጅግ ከባድ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አስታውቋል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

ድርጅቱ ባወጣው መረጃ በማዕከላዊ እና ሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ በሰሜን እና ማዕከላዊ የደቡብ ሱዳን አካባቢዎች እንዲሁም በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን ከ200 ሚሊሜትር በላይ የሆነ ከባድ ዝናብ ሊኖር ይችላል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ዛሬን ጨምሮ በፈረንጆቹ ሐምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንት ወትሮውኑ የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊከሰትል እንደሚችል ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ከስዊዘርላንድ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትብብር ታጠናክራለች” ለሊሴ ነሜ
Next articleበባቡር የሚጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ወደ ማሠራጫ ማዕከሎች እንዲደርስ በትኩረት እየተሠራ ነው።