የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።

68

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በታንዛንያ ዳሬሰላም ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው “የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት ማፋጠን፤ ወጣቶችን በትምህርት እና ክህሎቶች በማብቃት ምርታማነታቸውን ማሳደግ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ነው።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ በጉባኤው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በጉባኤው የአፍሪካ አገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ30 አገራት የተውጣጡ ከ1 ሺህ 200 በላይ ተሳታፊዎች ታድመዋል።

የሰው ኃይል ልማት በኢኮኖሚ እድገት እና ዜጋ ተኮር ኢንቨስትመንት ላይ ያለውን ፋይዳ የተመለከቱ ጉዳዮች በጉባኤው ላይ ይመከርባቸዋል።

በጉባኤው የአፍሪካ አገራት የሰው ኃይል ልማት ሥራዎች ተሞክሮ እንደሚቀርብ እና በዘርፉ ያሉ አዳዲስ እሳቤዎችን የተመለከቱ ሀሳቦች እንደሚንሸራሸሩ ተገልጿል።

ጉባኤው እስከ ነገ እንደሚቆይም ተጠቁሟል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዩኒቨርሲቲዎችን በትኩረት እና በተልእኮ በመለየት ለትምህርት ጥራት እየሠራን ነው” የትምህርት ሚኒስትር
Next articleኢትዮጵያ በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የመጀመሪያ ጨዋታዋን ዛሬ ከዩጋንዳ ጋር ታደርጋለች