ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሠሩ አሳሰቡ።

71

ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ኹኔታ ተመልክተዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ጋር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ተገኝተው ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹ ያለውን የተማሪ አቀባበል፣ የመኝታና የመመገቢያ ቦታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸውም ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሠሩ ሚኒስትሩ ማበረታታቸውን ኢዜአ ዘግበቧል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 19/2015 ጀምሮ ይሰጣል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፕሮፌሰሮች ወግ የተሰኘ መርሃ ግብር ተካሄደ።
Next articleፋሲል ከነማ ውበቱ አባተን አሠልጣኝ አድርጎ ሾመ።