
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሐመድ ያሲን በተፌ ወንዝ የመሻገሪያ ድልድይ ባለመገንባቱ እናትን ከልጇ የነጠለ፤ ልጅን ካለአባት ያስቀረ፤ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው የገታ፤ ማኅበረሰቡን ለከፍተኛ እንግልት የዳረገ ክስተት ላይደገም ዛሬ ላይ ፋይሉ ተዘግቷል ብለዋል።
እነሆ በዛሬው እለት በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰዴ ወረዳ ባለፉት ወራት ወደ ሥራ የገባው የተፌ ወንዝ ኮንክሪት ድልድይ ግንባታው ተጠናቆ በዚህ መልኩ መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ነው ያሉት።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሰዴ ወረዳ ማኅበረሰብ ልማትን ከመጠየቅ ባለፈ የራስን አቅም በማስተባበር እየሠሩት ያለው የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ እንዲሁም ልዩ ልዩ ስትራክቸር ግንባታ በተሞክሮነት የሚወሰድና እንዲሰፋ የሚደረግ ተግባር ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!