
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከአራቱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ2 መቶ በላይ የክረምት በጎ ፈቃድ ሰጭ ወጣቶች የሚሳተፉበት የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በንጉስ ተክለ- ሃይማኖት አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡
የከተማ አሥተዳደሩ ወጣቶች እና ሴቶች ሊግ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ደም ባንክ አገልግሎት ጋር በጋራ ባዘጋጁት የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በአንድ ቀን ሁለት መቶ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን የከተማ አሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!