
አዲስ አበባ: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት” ማስረጃ ውሳኔ ለመሥጠት ”በሚል መሪ መልዕክት የሚካሄደውን ዓለማቀፍ ጉባኤ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሠጡት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጥሩማር አባተ እንዳሉት ጉባኤው የሚያጋጥሙ ሀገራዊና አካባቢያዊ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረግ ሂደት የመረጃ አመንጭዎችንና ፓሊሲ ቀራጮችን ክፍተት መሙላትን ዓላማ ያደረገ ነው። በጉባኤው ችግሮችን የመቋቋምና መፍትሔ ማፍለቅ ልምዶች ይገኙበታልም ብለዋል።
በጉባኤው የመንግስት ዉሳኔ ሰጭዎች፣ ተመራማሪዎችና የሙያ ማኀበራት የሚሳተፉበት በመኾኑ ሀገራት ችግር ሲያጋጥማቸው የሚፈቱበት እና ማስረጃን የሚጠቀሙበትን መንገድ ልምድ ለመቅሰም እንደሚያስችልም ተገልጿል።
በጉባኤው አስር የአፍሪካ ሀገራትና አርባ ደግሞ ከሌሎች ክፍለ ዓለማት እንደሚሳተፋ ተገልጿል ።
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!