
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር በ2015 ዓ/ም በ124 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ መሠረተ ልማቶች የክልል፣ የብሔረሰብ አሥተዳደር፣ የወረዳና የከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት ተመረቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል ።
የተመረቁ መሠረተ ልማቶች ፦
በቀበሌ አንድ መንታ መንገድ ኮብል፣ በቀበሌ አራት ኮብል መንገድ ፣ በቀበሌ አምስት ሁለት የወጣቶች መዝናኛ ማዕከላትና ሌሎችም ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መመረቃቸውን የአዊ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!