ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን አልማ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት በእብናት ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ባለ ሦስት ፎቅ የመማሪያ ህንፃ በመንግስት እና በሕዝብ ተሳትፎ ተገንብቷል።
ለግንባታው 21 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል።
ህንጻውን የአልማን ሳምንት ምክኒያት በማድረግ ከፍተኛ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራሮች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ በተገኙበት መመረቁን የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!