
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች፡፡
ድጋፉ በዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ በዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር፣ በተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት እና በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አማካኝነት የሚሰራጭ ነው ተብሏል፡፡
ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች አስፈጊውን ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗም ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ እያሰራጩ ከሚገኙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እንደምትሰራ መገለጹንም በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ደቡብ ኮሪያ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፋ ማድረጓ ተጠቁሟል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!