
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ2015 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ተፈታኞቹን በመቀበል ላይ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው ከደቡብ ጎንደር ዞን ወረዳዎች የመጡ ደራ፣ አንዳቤት፣ ስማዳ፣ ሰዴ ሙጃ እና ፋርጣ ወረዳ የመጡ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወንድ 2203 ፣ሴት 2683 በድምሩ 4886 ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብሏል።
ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ቀናት በወጣላቸው የመግቢያ መርሃ ግብር መሰረት ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበሉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!