“ተጨማሪ ቁርጠኝነት እና የላቀ ትጋት የሚጠይቀን ጊዜ ላይ እንገኛለን” ኃይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር)

58

ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ኃይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር) ወቅታዊ የክረምት የግብርና ሥራዎችን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ዘዴዎችን ቆጥረን ይዘን በቁርጠኝነት ተግባራዊ ካደረግናቸው በምርት ዘመኑ ያቀድነውን 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት አሟጦ በዘር መሸፈን፣ አማካይ ምርታማነትን በሄክታር 31 ነጥብ 8 ኩንታል ማድረስ እና 160 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት በእርግጥም እናሳካዋለን ብለዋል።

ከማን፣ ምን እንደሚጠበቅ ዝርዝር ተግባራትን ያነሱት ዶክተር ኃይለማርያም የሚከተሉት አንኳር ጉዳዮች ገቢራዊ እንዲኾኑ አሳስበዋል።

🌾የሰው ሀይሉን በሙሉ አቅም ስምሪት መስጠት፣
🌾ተልዕኮን የመፈፀም ብቃት ማሳደግ
🌾በየስራ ዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት መረባረብ
🌾ችግርን በራስ አቅም የመፍታት ልምምድን ማዳበር
🌾አቅዶ የሚፈፅም ጠንካራ ተቋም መፍጠር
🌾በጊዜ ሰሌዳና አግሮ ኢኮሎጂን መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ
🌾ተከታታይነት ያለው የድጋፍና ክትትል ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገበባ ገልጸዋል።

መረጃው የአማራ ግብርና ቢሮ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄኔራል ብርሃኑ በቀለን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በባሕር ዳር ከተማ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ጎበኙ።
Next articleደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።