
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሞላሌ አዳባይ ያለውን የመንገድ የልማት ፕሮጀክት በመንዝ ማማ ምድር አስተዳደር አስተባባሪነት በደብረ ብርሃን ከተማ ውይይት ተደርጎበታል። በውይይቱም የደብረብርሃን ከተማ እና የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የፕሮጀክቱ ባለድርሻና ደጋፊ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ሀይሉ የአዳባይ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በርካታ ታሪካዊ ቦታዎችን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን መቅረፍ የሚችል ነው ብለዋል። 55 ኪ/ሜ የአዳባይ መንገድ ፕሮጀክት ከወረዳው የሚርቅ መሆኑን ጠቁመዋል አስተዳዳሪው ።
ፕሮጀክቱ በርካታ የሥራ እድል ፈጠራን የሚቀርፍ መኾኑንም አስታውሰዋል። የመንገድ ስራው ጥቅል 13 ነጥብ 5 ኪሎ ሜት መሆኑንም አንስተው 67 ሚሊዮን ብር በጀት የሚፈጅ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል አቶ መርሻ እስካሁን 4 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የጠረጋ ሥራ መሠራቱንም አብራርተዋል። 99 በመቶ የአዳባይ አሸዋ ጥራት እንዳለው በጥናት መረጋገጡንም ጠቁመዋል አቶ መርሻ።
በውይይቱም የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸ የአዳባይ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት የሸዋን የኢኮኖሚ የስነ ልቦና ውቅርን ፣ የይቻላል እሴትን የሚገነባ ነው ብለዋል። አዳባይ በርካታ ወረዳዎችን የሚያገናኝ ፣ በአሸዋ እጥረት የሸዋን የግንባታ ችግር የሚቀርፍ ለበርካታ ወጣቶች ቋሚ የሥራ እድል የሚፈጥር መሆኑንም ነው የጠቆሙት አቶ በድሉ ውብሸት። አዳባይ የሸዋ የማዕድን ፣ የግብርና እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ በርካታ ችግሮችን እንዲቀርፍ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከተማ አስተዳደሩ የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋልም በማለት የመክፈቻ ንግግራቸውን ቋጭተዋል አቶ በድሉ ውብሸት። የአዳባይን የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ለማሣለጥ የሚያስችል የፋይናንስ ምንጭ እቅድ፣ የፕሮጀክት አፈጻጸም እቅድ፣ እስካሁን የተደረሰበት የሥራ አፈጻጸም ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት መኾኑን የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!