
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሕገ-ወጥ ስደትን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ድህነትን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ግልጽ ተግባራት እንደሚያስፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በሰበሰቡት ዓለም አቀፍ የልማት እና የፍልሰት ኮንፈረንስ ላይ ዛሬ ተካፍለዋል።
ሕጋዊ የውጭ ሥራ ሥምሪት በሕጋዊ መልኩ ለወጡ የሥራ እና መተዳደሪያ ምንጭ፣ ለትውልድ ሀገራቸውም የሬሚታንስ ምንጭ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፣ ሕገ-ወጥ ፍልሰትን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ድህነትን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ግልጽ ተግባራት እንደሚያስፈልጉ አስምረዋል።
ለሥራ ፈጠራ ሙዓለ ንዋይን ማመቻቸት እንደሚገባ እና ለስደት በሚዳርጉ መነሻ ምክንያቶች ላይ መሥራት አስፈላጊ መሆኑንም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት አስገንዝበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!