
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከ30 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን በሶስቱም ግቢዎቹ እየተቀበለ ይገኛል።
በ2015 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ፣ በጤና ካምፓስ እና በቡሬ ካምፓስ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል ያደረገውን ሰፊ ዝግጅት በማጠናቀቅ ተፈታኞቹን በመቀበል ላይ እንደሚገኝ ከዩንቨርስቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!